በላይ ዘለቀ
በላይ ዘለቀና ወንድሞቹ ፦
ዘለቀ ላቀው (የበላይ ዘለቀ አባት ) የልጅ እያሱ አንጋች ነበሩ ። ልጅ እያሱ ሲገለበጡ ዘለቀ ላቀው ወደሚስታቸው አገር ወደ ጫቀታ ሄደው ልጆቻቸውን ይዘው ወደአገራቸው ወደ ለምጨን (ቢቸና ወረዳ ) ተሻገሩ ። (ቢቸና ጎጃም ውስጥ ጫቀታ ወሎ ውስጥ ከአባይ ወንዝ ማዶ ለማዶ ናቸው ። ይገበያያሉም ፡ ይጋባሉም ። )
በ1916 አ.ም. ማለት በላይ ዘለቀ የ14 አመት ልጅ ሳለ ፊታውራሪ እምቢ አለ የተባለ የራስ ሀይሉ ሌባ አዳኝ (ጸጥታ አስከባሪ ) ዘለቀ ላቀውን ከበባቸው ። ዘለቀ ላቀው እጄን አልሰጥም ስላሉ ተኩስ ተከፈተ ። ዘለቀ ላቀውና አብረዋቸው የነበረ አለሙ መርሻ የተባሉ ወንድማቸው ከአስር ሰው በላይ ገድለው ብዙ ሰው አቆሰሉ ።
«እኛ ልጆች ተኩስ ካባራ በህዋላ ተየጫካው ስንመለስ ሁለቱም ሞተዋል ። የዘለቀ ላቀው ሬሳ እበቱ በራፍ ላይ ተሰቅሎዋል ።» አሉ ፊታውራሪ ተሻለ አለሙ ። እንግዲህ በላይ ዘለቀና ተሻለ አለሙ እኩል አባቶቻቸውን አጡ ፡ አብረው የሀዘንን ጽዋ ቀመሱ ፡ እኩል በቀልን እያሰላሰሉ አደጉ ፡ በሁዋላም አብረው ጠላትን ተዋጉ ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ