YT_TheGeneration

                                                                            YaTewlidTheGeneration

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረት (ኢዴኃኅ)

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረት (ኢዴኃኅ) የተመሠረተው በጁላይ 26 እስከ ኦገስት 1, 2003 እ.አ.አ. አሜሪካ ውስጥ በተካሄደ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉባዔ ነው። ይህን ጉባዔ ለማዘጋጀት ሀሳቡ የመነጨው በኤፕሪል 2000 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሀገራዊ ጉባዔ የሚባለው የሲቪክ ድርጅትበተጠራና ሰባት የፖለቲካ ድርጅቶች በተገኙበት ሀሳብ የመለዋወጫ መድረክ ላይ ነበር። በተገኙት የፖለቲካ ድርጅቶች ስምምነት ተደርጎ አዘጋጅ ኮሚቴ ከተመሠረተ በኋላ የጉባዔው ዝግጅት ከሁለት ዓመት በላይ ወስዷል። በመጀመሪያ ስድስት አባላት የነበሩት በኋላም ወደ ዘጠኝ ከፍ ያለውና ከነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች የተውጣጣ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመስርቶ ለሁለት ዓመታት ያህል ድርጅቶችን በማነጋገር ሲያግባባና እንዲሁም ለጉባዔው ዝግጅት የቴክኒክና የፋይናንስ ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በኋላ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉባዔ ለመጥራት ተችሏል።

በዚህ ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የ15 የፖለቲካ ድርጅቶች ተወካዮች ለአንድ ሳምንት ያህል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተው ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ኅብረት (ኢዴኃኅ) እየተባለ የሚጠራውን የኅብረት አካል መስርተዋል።

ስለ ኢዴኃኅ የተለያዩ ሠነዶች ያላችሁ ትልኩልን ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

እትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Long Live Ethiopia!

......ያ ትውልድ......
ታሪካችሁ ህያው ነው!

The Generation is Immortal!

 

እኛን ማግኘት/Contact us

This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

703 300 4302